ዘሌዋውያን 1

የሚቃጠል መሥዋዕት 1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን ጠራው፤ ከመገናኛውም ድንኳን እንዲህ ሲል ተናገረው፤ 2 “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ከእናንተ ማንም ሰውለእግዚአብሔር(ያህዌ)ከእንስሳ ወገን መባ በሚያቀርብበት ጊዜ ከላሙ፣ ከበጉ፣ ወይም ከፍየሉ መንጋ መካከል ያቅርብ። 3 “ ‘መባው በሚቃጠል መሥዋዕትነት ከላሞች መንጋ…

ዘሌዋውያን 2

የእህል ቊርባን 1 “ ‘ማንኛውም ሰው የእህል ቊርባንለእግዚአብሔር(ያህዌ)በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ዱቄቱ የላመ ይሁን፤ ዘይት ያፍስበት፤ ዕጣንም ይጨምርበት፤ 2 ወደ ካህናቱም ወደ አሮን ልጆች ያምጣው። ካህኑ ከላመው ዱቄትና ከዘይቱ አንድ እፍኝ ሙሉ ያንሣለት፤ ዕጣኑንም ሁሉ ይውሰደው፤ ይህንም በእሳት…

ዘሌዋውያን 3

የኅብረት መሥዋዕት 1 “ ‘ማንኛውም ሰው የሚያቀርበው ቊርባን ከላሞች መንጋ የሚቀርብ የኅብረት መሥዋዕትከሆነ፣ እንከን የሌለበትን ተባዕት ወይም እንስትበእግዚአብሔር(ያህዌ)ፊት ያቅርብ። 2 በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይረደው፤ ካህናቱም የአሮን ልጆች ደሙን በመሠዊያው…

ዘሌዋውያን 4

የኀጢአት መሥዋዕት 1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፤ 2 “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፤ ‘ማንም ሰው ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፣እግዚአብሔር(ያህዌ)አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸውም አንዱን ተላልፎ ቢገኝ፣ 3 “ ‘የተቀባውም ካህን በሕዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኀጢአት ቢሠራ፣ ስለ ሠራው ኀጢአት እንከን…

ዘሌዋውያን 5

1 “ ‘አንድ ሰው ስላየውና ስለሚያውቀው ነገር ሕጋዊ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ተጠይቆ ቃሉን ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆን፣ ይህ ሰው ኀጢአት ሠርቶአልና ይጠየቅበታል። 2 “ ‘ማንኛውም ሰው ሳያውቅ በሥርዐቱ መሠረት የተከለከለውን ርኩስ ነገር ቢነካ፣ ይኸውም፦ የረከሰ የአውሬ በድን ወይም የረከሰ…

ዘሌዋውያን 6

1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 “ማንኛውም ሰው በዐደራ የተሰጠውን ወይም በመያዣነት የተቀበለውን በመካድና ባልንጀራውን በማጭበርበር ኀጢአት ቢሠራ፣እግዚአብሔርንም(ያህዌ)ቢበድል ወይም ባልንጀራውን ቢቀማው ወይም ቢያታልለው፣ 3 ወይም የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ቢል ወይም በሐሰት ቢምል ወይም ሰዎች የሚያደርጉትን…

ዘሌዋውያን 7

የበደል መሥዋዕት 1 “ ‘እጅግ ቅዱስ የሆነው የበደል መሥዋዕት የአቀራረብ ሥርዐት ይህ ነው፦ 2 የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የበደሉም መሥዋዕት እዚያው ይታረድ፤ ደሙም በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይረጭ። 3 ሥቡን በሙሉ ያቅርብ፤ ይኸውም፦ ላቱን፣ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን…

ዘሌዋውያን 8

አሮንና ልጆቹ ካህናት ሆነው መሾማቸው 1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 “አሮንንና ልጆቹን፣ ልብሰ ተክህኖውን፣ የመቅቢያ ዘይቱን፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን፣ ሁለቱን አውራ በጎችና እርሾ ሳይገባበት የተጋገረው ቂጣ ያለበትን መሶብ አምጣ፤ 3 ማኅበሩን በሙሉ በመገናኛው ድንኳን…

ዘሌዋውያን 9

ካህናቱ አገልግሎታቸውን ጀመሩ 1 በስምንተኛውም ቀን ሙሴ አሮንንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራቸው፤ 2 አሮንንም እንዲህ አለው፤ “የኀጢአት መሥዋዕት እንዲሆንልህ አንድ እንቦሳ እንዲሁም የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲሆንልህ አንድ አውራ በግ፣ ወስደህ፣በእግዚአብሔር(ያህዌ)ፊት አቅርባቸው፤ ሁለቱም እንከን የሌለባቸው ይሁኑ።…

ዘሌዋውያን 10

የናዳብና የአብዩድ መሞት 1 የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናዎቻቸውን ወስደው ፍም አደረጉባቸው፤ ዕጣንም ጨመሩባቸው፤ እርሱ ያላዘዛቸውን፣ ያልተፈቀደውን እሳትበእግዚአብሔር(ያህዌ)ፊት አቀረቡ። 2 ከዚህም የተነሣ እሳትከእግዚአብሔር(ያህዌ)ዘንድ ወጥቶ በላቸው፤በእግዚአብሔርም(ያህዌ)ፊት ሞቱ። 3 ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር(ያህዌ)፦ ‘ወደ እኔ…