ዘዳግም 22

1 የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታየው፣ ወደ እርሱ መልሰህ አምጣለት እንጂ ዝም ብለህ አትለፈው፤ 2 ወንድምህ በአቅራቢያህ ባይኖር፣ ወይም የማን መሆኑን የማታውቅ ከሆነ፣ ባለቤቱ ፈልጎት እስኪመጣ ድረስ፣ ወደ ቤትህ ወስደህ ከአንተ ዘንድ አቈየው፤…

ዘዳግም 23

ከእግዚአብሔር ጉባኤ መለየት 1 ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቈረጠ ማናቸውም ሰው ወደእግዚአብሔር(ያህዌ)ጉባኤ አይግባ። 2 ዲቃላም ይሁን የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ፣ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደእግዚአብሔር(ያህዌ)ጉባኤ አይግባ። 3 አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፣…

ዘዳግም 24

1 አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ፣ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት፣ የፍቺ ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት። 2 ከቤቱ ከወጣች በኋላ ሌላ ባል ብታገባ፣ 3 ሁለተኛ ባሏም እንደዚሁ ጠልቷት የፍቺ ወረቀት በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ…

ዘዳግም 25

1 በሰዎች መካከል ጠብ ቢነሣና ወደ ፍርድ አደባባይ ቢሄዱ፣ ዳኞች ተበዳይን ነጻ፣ በዳይን ግን ጥፋተኛ በማድረግ የፍርድ ውሳኔ ይስጡ። 2 በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ፣ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፤ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ…

ዘዳግም 26

ዐሥራትና በኵራት 1 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፣ ስትወርሳትና ስትኖርባት፣ 2 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰ በስበው ሰብል ሁሉ፣ በኵራት ወስደህ በቅርጫት ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ፤ 3 በዚያም ወቅት…

ዘዳግም 27

በጌባል ተራራ ላይ የቆመ መሠዊያ 1 ሙሴና የእስራኤል አለቆች ሕዝቡን እንዲህ ብለው አዘዙ፤ “ዛሬ የማዛችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ፤ 2 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፣ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁምና በኖራ ቅባቸው። 3 የአባቶችህ…

ዘዳግም 28

በመታዘዝ የሚገኝ በረከት 1 ለአምላክህለእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በፍጹም ብትታዘዝና እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙን ሁሉ በጥንቃቄ ብትከተል፣ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በምድር ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ያደርግሃል። 2 አምላክህንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ብትታዘዝ፣ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ያንተ ይሆናሉ፤ አይለዩህምም። 3 በከተማ ትባረካለህ፣…

ዘዳግም 29

የቃል ኪዳኑ መታደስ 1 እግዚአብሔር(ያህዌ)በኮሬብ ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞዓብ ምድር ከእስራኤላውያን ጋር እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው የኪዳኑ ቃሎች እነዚህ ናቸው። 2 ሙሴ እስራኤላውያንን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔር(ያህዌ)በግብፅ፣ በፈርዖን፣ በሹማምቱ ሁሉና በመላ አገሩ ላይ ያደረገውን…

ዘዳግም 30

ወደ እግዚአብሔር በመመለስ የሚገኝ በረከት 1 በፊትህ ያስቀመጥሁት ይህ በረከትና መርገም ሁሉ በአንተ ላይ ሲመጣና አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በትኖህ በምትኖርበት አሕዛብ መካከል ሆነህ ወደ ልብህ ተመልሰህ ነገሮቹን በምታስተውልበት ጊዜ፣ 2 እንዲሁም ዛሬ እኔ በማዝህ ሁሉ መሠረት አንተና…

ዘዳግም 31

ኢያሱ በሙሴ እግር መተካቱ 1 ከዚያም ሙሴ ወጥቶ እነዚህን ቃሎች ለእስራኤል ሁሉ ተናገረ፤ 2 “እነሆ፤ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከእንግዲህ ልወጣና ልገባ አልችልም፤እግዚአብሔርም(ያህዌ)‘ዮርዳኖስን አትሻገርም’ ብሎኛል፤ 3 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ራሱ በፊትህ ቀድሞ ይሄዳል፤ እነዚህንም አሕዛብ ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤…