ዘፀአት 1

እስራኤላውያን በጭቆና ሥር 1 ቤተ ሰቦቻቸውን ይዘው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የሄዱት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፦ 2 ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ 3 ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ብንያም፣ 4 ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር። 5 የያዕቆብ ዘር ጠቅላላ…

ዘፀአት 2

የሙሴ መወለድ 1 በዚያን ጊዜ ከሌዊ ነገድ የሆነ አንድ ሰው አንዲት ሌዋዊት ሴት አገባ። 2 እርሷም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሕፃኑ መልከ መልካም መሆኑን ባየች ጊዜ ሦስት ወር ሸሸገችው። 3 ከዚያ በላይ ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ…

ዘፀአት 3

ሙሴና የሚንበለበለው ቍጥቋጦ 1 አንድ ቀን ሙሴ የምድያም ካህን የሆነውን የአማቱን የዮቶር በጎችና ፍየሎች እየጠበቀ ሳለ፣ መንጋውን እየነዳ ወደ ምድረ በዳው ዳርቻ አምርቶ የእግዚአብሔር(ኤሎሂም)ተራራ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ኮሬብ ቀረበ። 2 እዚያምየእግዚአብሔር(ያህዌ)መልአክ በቍጥቋጦው ውስጥ በሚንቀለቀል የእሳት…

ዘፀአት 4

ለሙሴ የተሰጡ ምልክቶች 1 ሙሴም “ባያምኑኝስ፤ ቃሌን ባይቀበሉስ፤ ‘እግዚአብሔር(ያህዌ)አልተገለጠልህም’ ቢሉኝስ?” ብሎ መለሰ። 2 እግዚአብሔርም(ያህዌ)፣ “በእጅህ የያዝሀት እርሷ ምንድን ናት?” ሲል ጠየቀው፤ እርሱም መልሶ፣ “በትር ናት” አለው። 3 እግዚአብሔርም(ያህዌ)፣ “መሬት ላይ ጣላት” አለው። ሙሴ በትሩን መሬት…

ዘፀአት 5

ጭድ አልባ ሸክላ 1 ከዚህ በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ “የእስራኤል አምላክእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ይላል” አሉት። 2 ፈርዖንም “እንድታዘዘውና እስራኤልን እንድለቅለት ለመሆኑ ይህእግዚአብሔር(ያህዌ)ማነው?”እግዚአብሔርን(ያህዌ)አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ። 3 እነርሱም፣ “የዕብራውያን አምላክ(ኤሎሂም)ለእኛ…

ዘፀአት 6

1 ከዚያምእግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን፣ “አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ፤ ከኀያሉ እጄ የተነሣ እንዲሄዱ፣ ይለቃቸዋል፤ ከኀያሉም እጄ የተነሣ ከአገሩ ያስወጣቸዋል” አለው። 2 እግዚአብሔርም(ኤሎሂም)ሙሴን አለው፤ “እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ። 3 ሁሉን የሚችል አምላክ(ኤሎሂም)ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግንእግዚአብሔር(ያህዌ)በተባለው ስሜራሴን አልገለጥሁላቸውም። 4…

ዘፀአት 7

1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ልብ በል፤ እኔ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ(ኤሎሂም)አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህ አሮንም ያንተ ነቢይ ይሆናል። 2 እኔ የማዝህን ሁሉ ትናገራለህ፤ ወንድምህ አሮንም እስራኤላውያንን ከአገሩ እንዲወጡ ይለቃቸው ዘንድ ለፈርዖን ይነግረዋል። 3 እኔ ግን የፈርዖንን ልብ…

ዘፀአት 8

የጓጒንቸር መቅሠፍት 1 ከዚያምእግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን አለው፤ “ወደ ፈርዖን ዘንድ ሄደህ፣ እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር(ያህዌ)የሚለው ይህ ነው፤ “እኔን ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ። 2 እነርሱን ለመልቀቅ እምቢ ብትል አገርህን ሁሉ በጓጒንቸር መቅሠፍት እመታዋለሁ። 3 አባይ በጓጒንቸሮች ይሞላል፤ ወጥተውም ወደ…

ዘፀአት 9

የእንስሳት እልቂት 1 ከዚያምእግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ በለው፤ ‘የዕብራውያን አምላክ(ኤሎሂም)እግዚአብሔር(ያህዌ)የሚለው ይህ ነው፤ “ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።” 2 አሁንም እንዳይሄዱ ብታደርግና ብትከለክላቸው፣ 3 የእግዚአብሔር(ያህዌ)እጅ በመስክ ላይ ባሉት እንስሳት፣ በፈረሶችህና በአህዮችህ፣ በግመሎችህና በቀንድ ከብቶችህ፣…

ዘፀአት 10

የአንበጣ መንጋ መቅሠፍት 1 ከዚያምእግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ተመልሰህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እነዚህን ታምራዊ ምልክቶች በመካከላቸው ለማድረግ የፈርዖንንና የሹማምቱን ልብ አደንድኛለሁና፤ 2 ይኸውም ግብፃውያንን እንዴት አድርጌ እንደ ቀጣኋቸውና በመካከላቸውም ምልክቶቼን እንዴት እንዳደረግሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ እንድትነግሩና…