ይሁዳ 1

1 የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ፤ ለተጠሩት፣ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዱትና በኢየሱስ ክርስቶስ ለተጠበቁት፤ 2 ምሕረት፣ ሰላምና ፍቅር ይብዛላችሁ። የዐመፀኞች ኀጢአትና የሚጠብቃቸው ፍርድ 3 ወዳጆች ሆይ፤ አብረን ስለምንካፈለው ድነት ልጽፍላችሁ እጅግ ጓጒቼ ነበር፤ ነገር ግን…