1 ቆሮንቶስ 10

በእስራኤል የደረሰው እንዳይደርስብን እንጠንቀቅ 1 ወንድሞች ሆይ፤ አባቶቻችን ሁሉ ከደመናው በታች እንደ ነበሩና በባሕሩ ውስጥ እንደ ተሻገሩ ታውቁ ዘንድ እፈልጋለሁ። 2 እነርሱ ሁሉ ከሙሴ ጋር ለመተባበር በደመናና በባሕር ተጠመቁ። 3 ሁሉም ከአንድ መንፈሳዊ ምግብ በሉ፤…

1 ቆሮንቶስ 11

1 እኔ የክርስቶስን ምሳሌ እንደምከተል እናንተም የእኔን ተከተሉ። ሥርዐት ያለው አምልኮ 2 በሁሉም ነገር ስለምታስቡልኝና ከእኔ የተቀበላችሁትን ትምህርትአጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ። 3 ነገር ግን ይህን እንድታውቁ እወዳለሁ፤ የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ ነው፤ የሴትም ራስ ወንድ…

1 ቆሮንቶስ 12

መንፈሳዊ ስጦታዎች 1 ወንድሞች ሆይ፤ አሁን ደግሞ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ይህን እንድታውቁ እፈልጋለሁ። 2 አረማውያን በነበራችሁበት ጊዜ ወዲያና ወዲህ በመነዳት ድዳ ወደ ሆኑ ጣዖታት እንደ ተወሰዳችሁ ታውቃላችሁ። 3 ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ የሚናገር፣ “ኢየሱስ የተረገመ…

1 ቆሮንቶስ 13

1 በሰዎችና በመላእክት ልሳንብናገር፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚ ጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ። 2 የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ ምስጢርን ሁሉና ዕውቀትን ሁሉ ባውቅ፣ ተራራንም ከቦታው የሚነቅል እምነት ቢኖረኝ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። 3 ያለኝን…

1 ቆሮንቶስ 14

የትንቢትና የልሳን ስጦታዎች 1 ፍቅርን ተከታተሉ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን፣ በተለይም ትንቢት የመናገርን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ። 2 በልሳንየሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርምና፤ ምስጢር የሆነውን በመንፈስስለ ሚናገር የሚረዳው የለም። 3 ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽ፣ ለማበረታታትና ለማጽናናት ለሰው ይናገራል።…

1 ቆሮንቶስ 15

የክርስቶስ ትንሣኤ 1 አሁንም፣ ወንድሞች ሆይ፤ የሰበክ ሁላችሁንና የተቀበላችሁትን ደግሞም ጸንታችሁ የቆማችሁበትን ወንጌል ላሳስባችሁ እወዳለሁ፤ 2 የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣ በዚህ ወንጌል ትድናላችሁ፤ አለዚያ ያመናችሁት በከንቱ ነው። 3 እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውንለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት…

1 ቆሮንቶስ 16

ለቅዱሳን የተደረገ የገንዘብ መዋጮ 1 አሁን ደግሞ ለቅዱሳን ስለሚደረገው ገንዘብ ማሰባሰብ፤ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት በሰጠሁት ትእዛዝ መሠረት አድርጉ። 2 ገንዘብ ማሰባሰብ የሚደረገው እኔ በምመጣበት ጊዜ እንዳይሆን፣ ከእናንተ እያንዳንዱ እንደ ገቢው መጠን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እየለየ…

2 ቆሮንቶስ 1

1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ ከወንድማችንም ከጢሞቴዎስ፤ በቆሮንቶስ ላለችው ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ፤ 2 ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። የመጽናናት አምላክ 3 የርኅራኄ…

2 ቆሮንቶስ 2

1 እንግዲህ ላሳዝናችሁ ስላልፈለግሁ ወደ እናንተ ዳግመኛ ላለመምጣት ወሰንሁ፤ 2 እኔ ባሳዝናችሁም እንኳ፣ ከእናንተው ካሳዘንኋችሁ በቀር ደስ የሚያሰኘኝ ማን አለ? 3 ባለፈው ጊዜ እንደዚያ የጻፍሁላችሁ ወደ እናንተ ስመጣ ደስ ሊያሰኙኝ የሚገባቸው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ በማለት ነው፤…

2 ቆሮንቶስ 3

1 እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎቹ ለእናንተ ወይም ከእናንተ የተጻፈ የምስጋና ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆንን? 2 እናንተኮ ሰው ሁሉ የሚያውቃችሁና የሚያነባችሁ በልባችን ላይ የተጻፋችሁ ደብዳቤዎቻችን ናችሁ፤ 3 እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ፣…