ዘኁልቍ 4

ቀዓታውያን 1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ 2 “ከሌዋውያን ወገን የቀዓት ዘር የሆኑትን በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ቊጠሩ። 3 እንዲሁም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡትን ከሠላሳ እስከ አምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቊጠሩ። 4 “በመገናኛው…

ዘኁልቍ 5

የሰፈሩ መንጻት 1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 “ተላላፊ የቆዳ በሽታያለበትን ወይም ማንኛውም ዐይነት ፈሳሽ ከሰውነቱ የሚወጣውን ወይም ሬሳ በመንካቱ በሥርዐቱ መሠረት የረከሰውን ሰው ሁሉ ከሰፈር እንዲያስወጡ እስራኤላውያንን እዘዝ፤ 3 ወንድም ሆነ ሴት አስወጡ፤ እኔ በመካከላቸው…

ዘኁልቍ 6

የናዝራዊነት ሥርዐት 1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፣ ‘ወንድም ሆነ ሴት ናዝራዊ ይሆን ዘንድ ራሱንለእግዚአብሔር(ያህዌ)ለመለየት ስእለት ቢሳል፣ 3 ከወይን ጠጅና ከሌላም ከሚያሰክር መጠጥ ይታቀብ፤ የወይንም ሆነ የሚያሰክር የሌላ መጠጥ ኾምጣጤ አይጠጣ፤ እንዲሁም…

ዘኁልቍ 7

ማደሪያው ድንኳን ሲመረቅ የቀረቡ ስጦታዎች 1 ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑን ተክሎ ካበቃ በኋላ ማደሪያ ድንኳኑንና ዕቃዎቹን ሁሉ ቀባቸው፤ ቀደሳቸውም፤ እንደዚሁም መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ ቀባቸው፤ ቀደሳቸውም። 2 ከዚያም የእስራኤል አለቆች ሆነው ከተቈጠሩት ነገዶች ኀላፊዎች የነበሩት የየቤተ ሰቡ…

ዘኁልቍ 8

የመብራቶቹ አቀማመጥ 1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 “አሮንን ተናገረው፤ እንዲህም በለው፤ ‘ሰባቱን መብራቶች በየቦታቸው በምታስቀምጥበት ጊዜ በመቅረዙ ፊት ለፊት ላለው አካባቢ ብርሃን ይሰጣሉ።’ ” 3 አሮንም እንዲሁ አደረገ፤እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን ባዘዘው መሠረት መብራቶቹ በመቅረዙ ላይ ሆነው ፊት ለፊት…

ዘኁልቍ 9

የፋሲካ በዓል 1 ከግብፅ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወርእግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን በሲና ምድረ በዳ ተናገረው፤ እንዲህም አለው፤ 2 “እስራኤላውያን በተወሰነው ጊዜ የፋሲካን በዓል እንዲያከብሩ አድርግ፤ 3 በዓሉንም በዚህ ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ በተወሰነው…

ዘኁልቍ 10

የብር መለከቶች 1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 “ከተቀጠቀጠ ብር ሁለት መለከት አብጅ፤ ማኅበረ ሰቡን ለመጥሪያና ከሰፈራቸው እንዲነሡም ለመቀስቀሻ አድርጋቸው። 3 ሁለቱ መለከቶች ሲነፉ ማኅበረ ሰቡ በሙሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አንተ ዘንድ ይሰብሰብ፤ 4 ነገር ግን…

ዘኁልቍ 11

ከእግዚአብሔር የወረደ እሳት 1 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ስለ ደረሰባቸው ችግርበእግዚአብሔር(ያህዌ)ላይ አጒረመረሙ፤እግዚአብሔርም(ያህዌ)ማጒረም ረማቸውን በሰማ ጊዜ በጣም ተቈጣ፤ ከዚያምየእግዚአብሔር(ያህዌ)እሳት በመካከላቸው ነደደች፤ ከሰፈሩም ዳርቻ ጥቂቱን በላች። 2 ሕዝቡ ወደ ሙሴ ጮኸ፤ ሙሴም ወደእግዚአብሔር(ያህዌ)ጸለየ፤ እሳቲቱም ጠፋች። 3 ከዚህ የተነሣም…

ዘኁልቍ 12

ማሪያምና አሮን ሙሴን ተቃወሙ 1 ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት አግብቶ ነበርና ባገባት ኢትዮጵያዊት ምክንያት ማርያምና አሮን ይነቅፉት ጀመር። 2 እነርሱም፣ “ለመሆኑእግዚአብሔር(ያህዌ)የተናገረው በሙሴ አማካይነት ብቻ ነውን? በእኛስ አልተናገረም?” ተባባሉ፤እግዚአብሔርም(ያህዌ)ይህን ሰማ። 3 ሙሴ በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ…

ዘኁልቍ 13

ከነዓንን መሰለል 1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 “ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ጥቂት ሰዎች ላክ፤ ከእያንዳንዱም የአባቶች ነገድ አለቃ ይላክ።” 3 ስለዚህ ሙሴበእግዚአብሔር(ያህዌ)ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ እነዚህን ላካቸው፤ ሁሉም የእስራኤላውያን አለቆች ነበሩ፤ 4 ስማቸውም እንደሚከተለው…