2 ሳሙኤል 15

የአቤሴሎም ዐመፅ 1 ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ሠረገላና ፈረሶች እንዲሁም ፊት ፊቱ የሚሮጡ አምሳ ሰዎች ለራሱ አዘጋጀ። 2 አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ሆን ብሎ ይቆም ነበር። ማናቸውም ባለ ጒዳይ አቤቱታውን…

2 ሳሙኤል 16

ዳዊትና ሲባ 1 ዳዊት ከተራራው ጫፍ ባሻገር ጥቂት እልፍ ብሎ እንደሄደ፣ ሲባ የተባለው የሜምፊቦስቴ አገልጋይ፣ ሁለት መቶ እንጀራ፣ አንድ መቶ ጥፍጥፍ ዘቢብ፣ አንድ መቶ ጥፍጥፍ በለስና አንድ አቍማዳ የወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች እየነዳ ሊገናኘው…

2 ሳሙኤል 17

1 አኪጦፌልም፣ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰው መርጬ፣ በዛሬዪቱ ሌሊት አባትህን አሳድደዋለሁ፤ 2 በደከመውና ዐቅም ባነሰው ጊዜም አደጋ እጥልበታለሁ፤ ሽብር እለቅበታለሁ፤ ከዚያም አብሮት ያለው ሕዝብ ሁሉ ትቶት ይሸሻል፤ ንጉሡን ብቻ እመታዋለሁ፣ 3 ሕዝቡን…

2 ሳሙኤል 18

የአቤሴሎም መሞት 1 ዳዊት አብሮት የነበረውን ሕዝብ ቈጠረ፤ የሻለቆችንና የመቶ አለቆችን ሾመላቸው። 2 ዳዊትም ሰራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፣ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩያ ልጅ በአቢሳ፣ ሲሦውን ደግሞ በጌታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው። ንጉሡም ለሰራዊቱ፣ “እኔ ራሴም አብሬአችሁ…

2 ሳሙኤል 19

1 ለኢዮአብ፣ “ንጉሡ ዳዊት ስለ ልጁ ስለ አቤሴሎም እያለቀሰ እያዘነ ነው” ተብሎ ተነገረው። 2 ንጉሡ፣ “ስለ ልጁ አዝኖአል” መባሉን በዚያ ቀን ሰራዊቱ ሰምቶ ስለ ነበር፣ የዚያ ዕለት ድል በመላው ሰራዊት ዘንድ ወደ ሐዘን ተለውጦ ዋለ።…

2 ሳሙኤል 20

ሳቤዔ በዳዊት ላይ ዐመፀ 1 በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የተባለ አንድ ምናምንቴ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ…

2 ሳሙኤል 21

የገባዖናውያን ብቀላ 1 በዳዊት ዘመነ መንግሥት፣ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊትእግዚአብሔርንጠየቀ፤እግዚአብሔርም፣ ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፣ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ። 2 ንጉሡ ገባዖናውያንን ጠርቶ አነጋገራቸው። ገባዖናውያን ከአሞራውያን የተረፉ እንጂ ከእስራኤል ወገን አልነበሩም፤…

2 ሳሙኤል 22

የዳዊት የምስጋና መዝሙር 1 እግዚአብሔርከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦልም እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃልለእግዚአብሔርዘመረ፤ 2 እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔርዐለቴ ዐምባዬና ታዳጊዬ ነው፤ 3 አምላኬ፣ የምጠጋበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድነው። እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ ከኀይለኞች…

2 ሳሙኤል 23

የዳዊት የመጨረሻ ቃል 1 የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው፤ “በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣ ልዑል ከፍ ከፍ ያደረገው ሰው፣ የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ፣ የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤ 2 “የእግዚአብሔርመንፈስ በእኔ ተናገረ፤ ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ።…

2 ሳሙኤል 24

ዳዊት ተዋጊዎቹን ቈጠረ 1 እንደ ገናምእግዚአብሔርበእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ዳዊትንም በእነርሱ ላይ በማስነሣት፣ “ሂድ እስራኤልንና ይሁዳን ቊጠር” አለው። 2 ስለዚህም ንጉሡ ኢዮአብንና አብረውት ያሉትን የጦር አዛዦች፣ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፤ ብዛታቸው…