ኢዮብ 6

ኢዮብ 1 ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤ 2 “ምነው ሐዘኔ በተመዘነ! መከራዬም ሚዛን ላይ በተቀመጠ! 3 ከባሕር አሸዋ ይልቅ በከበደ፣ ኀይለ ቃሌም ባላስገረመ ነበር! 4 ሁሉን የሚችል አምላክ ፍላጻ በውስጤ ነው፤ መንፈሴም መርዙን ትጠጣለች፤ የእግዚአብሔር ማስደንገጥ…

ኢዮብ 7

1 “የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ተጋድሎ አይደለምን? ዘመኑስ እንደ ምንደኛ ዘመን አይደለምን? 2 የምሽትን ጥላ እንደሚመኝ አገልጋይ፣ ደመወዙንም እንደሚናፍቅ ምንደኛ፣ 3 እንዲሁ ከንቱ ወራት ታደሉኝ፣ የጒስቍልና ሌሊቶችም ተወሰኑልኝ። 4 በተኛሁ ጊዜ ‘መቼ ነግቶ እነሣለሁ?’…

ኢዮብ 8

በልዳዶስ 1 ሹሐዊውም በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ 2 “እንዲህ ያለውን ነገር የምትናገረው፣ ቃልህም እንደ ብርቱ ነፋስ የሚሆነው እስከ መቼ ነው? 3 እግዚአብሔር ፍትሕን ያጣምማልን? ሁሉን ቻይ አምላክስ ጽድቅን ያጣምማልን? 4 ልጆችህ በእርሱ ላይ ኀጢአት ሠርተው…

ኢዮብ 9

ኢዮብ 1 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ 2 “በእርግጥ ነገሩ እንዲህ እንደሆነ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ሥጋ ለባሽ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ ሊሆን ይችላል? 3 ሰው ከእርሱ ጋር ለመከራከር ቢፈልግ፤ ከሺህ ጥያቄ እንዱን እንኳ መመለስ አይችልም። 4…

ኢዮብ 10

1 “ሕይወቴን እጅግ ጠላሁ፤ ስለዚህም ማጒረምረሜን ያለ ገደብ እለቃለሁ፤ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ። 2 እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፤ በምን ላይ እንዳልተስማማን ንገረኝ እንጂ አትፍረድብኝ። 3 የክፉዎችን ዕቅድ በደስታ እየተቀበልህ፣ እኔን ግን ስታስጨንቀኝ፣ የእጅህንም ሥራ ስታዋርድ ደስ ይልሃልን?…

ኢዮብ 11

ሶፋር 1 ነዕማታዊው ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፤ 2 “ይህ ሁሉ ቃል መልስ ማግኘት አይገባውምን? ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ እውነተኛ ይቈጠርን? 3 በውኑ የአንተ መዘላበድ ሰውን ዝም ያሰኛልን? ስታፌዝስ የሚገሥጽህ የለም? 4 እግዚአብሔርንም፣ ‘ትምህርቴ የጠራ፤ በዐይንህም…

ኢዮብ 12

ኢዮብ 1 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ 2 “በእርግጥ ሰው ማለት እናንተ ናኋ! ጥበብም ከእናንተ ጋር ትሞታለቻ! 3 ነገር ግን እኔም እንደ እናንተ አእምሮ አለኝ፤ ከእናንተ አላንስም፤ እንዲህ ያለውን ነገር የማያውቅ ማን ነው? 4 እግዚአብሔርን ጠርቼ…

ኢዮብ 13

1 “ይህን ሁሉ ዐይኔ አይቶአል፤ ጆሮዬም ሰምቶ አስተውያለሁ፤ 2 እናንተ የምታውቁትን፣ እኔም ዐውቃለሁ፤ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም። 3 ነገር ግን ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ፤ ከእግዚአብሔርም ጋር መዋቀስ እሻለሁ። 4 እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናቸሁ፤…

ኢዮብ 14

1 “ከሴት የተወለደ ሰው፣ ዘመኑ አጭርና በመከራ የተሞላ ነው፤ 2 እንደ አበባ ይፈካል፤ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላ ይፈጥናል፤ አይጸናምም። 3 እንደዚህ ባለ ሰው ላይ ዐይንህን ታሳርፋለህን? ለፍርድስ በፊትህ ታቀርበዋለህን? 4 ከርኩስ ነገር ውስጥ ንጹሕን ማን ሊያወጣ…

ኢዮብ 15

ኤልፋዝ 1 ቴማናዊው ኤልፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ፤ 2 “ጠቢብ ሰው በከንቱ ንግግር መልስ ይሰጣልን? ወይስ በምሥራቅ ነፋስ ሆዱን ይሞላል? 3 በማይረባ ቃል፣ ፍሬ ቢስ በሆነም ንግግር ይከራከራልን? 4 አንተ ግን እግዚአብሔርን መፍራት ታጣጥላለህ፤ አምልኮተ እግዚአብሔርን…