መዝሙር 4

የሠርክ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዜም የዳዊት መዝሙር 1 የጽድቄ አምላክ ሆይ፤ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤ ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤ ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ። 2 ሰዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ዝቅታደርጋላችሁ? እስከ መቼስ ድረስ ከንቱ ነገርን ትወዳላችሁ? ሐሰትንስትሻላችሁ?ሴላ…

መዝሙር 5

የጧት ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ በዋሽንት የሚዘመር፣ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ቃሌን አድምጥ፤ መቃተቴንም ቸል አትበል። 2 ንጉሤና አምላኬ ሆይ፤ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ ድረስልኝ ብዬ ስጮህ ስማኝ። 3 እግዚአብሔርሆይ፤ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤ በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ፤…

መዝሙር 6

በጭንቅ ጊዜ የቀረበ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር በሸሚኒት 1 እግዚአብሔርሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ። 2 እግዚአብሔርሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤ እግዚአብሔርሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ። 3 ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤ እስከ መቼ፤ አንተእግዚአብሔርሆይ፤ ይህ…

መዝሙር 7

በስደት ጊዜ የጻድቁ ሰው ጸሎት ዳዊት በብንያማዊው በኩዝ ምክንያት ለእግዚአብሔር የዘመረው መዝሙር 1 እግዚአብሔርአምላኬ ሆይ፤ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም፤ 2 አለበለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤ የሚያድነኝ በሌለበትም ይቦጫጭቁኛል። 3 እግዚአብሔርአምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ…

መዝሙር 8

የፈጣሪ ግርማ በፍጥረቱ ላይ ለመዘምራን አለቃ፣ በዋሽንት የሚዜም፤ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔርአምላካችን ሆይ፤ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው! ክብርህ ከሰማያት በላይ፣ ከፍ ከፍ ብሎአል። 2 ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ፣ ምስጋናንአዘጋጀህ፤ ከጠላትህ የተነሣ፣…

መዝሙር 9

በክፉ ላይ ፍርድ ለመዘምራን አለቃ፤ በሙትላቤን ቅኝት፤ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔርሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስለ ድንቅ ሥራዎችህም ሁሉ እናገራለሁ። 2 በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ። 3 ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ…

መዝሙር 10

ለፍትሕ የቀረበ ልመና 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ለምን እንዲህ ርቀህ ቆምህ? በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ? 2 ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤ በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ። 3 ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ ስግብግቡን ይባርካል፤እግዚአብሔርንምይዳፈራል። 4 ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ…

መዝሙር 11

የጻድቃን ትምክሕት ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር 1 በእግዚአብሔርታምኛለሁ፤ ታዲያ ነፍሴን፣ “እንደ ወፍ ወደ ተራራ ብረሪ” ለምን ትሏታላችሁ? 2 ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ? “ክፉዎች፣ እነሆ፣ ቀስታቸውን ገትረዋል፤ የቅኑን ሰው ልብ በጨለማ ለመንደፍ፣ ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።…

መዝሙር 12

ከክፉ ዓለም ለመዳን የቀረበ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ በስምንተኛው ቅኝት የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር። 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ደግ ሰው የለምና አንተው ድረስልኝ! ከሰዎችም መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም። 2 እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ፤…

መዝሙር 13

በአምላኩ የታመነ ሰው አቤቱታ ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር። 1 እግዚአብሔርሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ለዘላለሙ ትረሳኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው እስከ መቼ ድረስ ነው? 2 ከሐሳቤ ጋር የምሟገተው፣ ልቤም ቀኑን ሙሉ የሚያዝነው እስከ መቼ ነው? ጠላቴስ በእኔ…