መዝሙር 54

ለፍትሕ አምላክ የቀረበ አቤቱታ ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች፤ ዜፋውያን ወደ ሳኦል መጥተው፣ “ዳዊት በእኛ ዘንድ ተደብቆአል” ባሉት ጊዜ፤ የዳዊት ትምህርት። 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ አድነኝ፤ በኀይልህም ፍረድልኝ። 2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማልኝ፤ የአፌንም ቃል አድምጥ። 3…

መዝሙር 55

በስደት ጊዜ የቀረበ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች፤ የዳዊት ትምህርት 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ልመናዬን ቸል አትበል፤ 2 ወደ እኔ ተመልከት፤ መልስልኝም። በውስጤ ታውኬአለሁ፤ ተናውጬአለሁም፤ 3 በጠላት ድምፅ ተሸበርሁ፤ በክፉዎች ድንፋታ ደነገጥሁ፤ መከራ አምጥተውብኛልና፤ በቍጣም…

መዝሙር 56

በእግዚአብሔር መደገፍ ለመዘምራን አለቃ፤ “ርግቢቱ ሩቅ ባለው ወርካ ላይ” በተባለው ቅኝት፤ ፍልስጤማውያን በጌት በያዙት ጊዜ፤ የዳዊት ቅኔ 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰዎች መረገጫ ሆኛለሁና ማረኝ፤ ቀኑንም ሙሉ በውጊያ አስጨንቀውኛል። 2 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ፤ በትዕቢት…

መዝሙር 57

በጨካኝ ጠላቶች ዘንድ ለመዘምራን አለቃ፤ “አታጥፋ” በሚለው ቅኝት የሚዘመር፤ ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ፤ የዳዊት ቅኔ። 1 ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረኝ፤ ነፍሴ አንተን መጠጊያ አድርጋለችና፤ በክንፎችህ ሥር እጠለላለሁ። 2 ለእኔ ያሰበውን ወደሚፈጽምልኝ አምላክ፣ ወደ…

መዝሙር 58

የምድር ዳኞች ፈራጅ ለመዘምራን አለቃ፤ “አታጥፋ” በሚለው ቅኝት የሚዘመር፤ የዳዊት ቅኔ 1 ኀያላን ሆይ፤ በውኑ ጽድቅ ከአፋችሁ ይወጣል? የሰው ልጆች ሆይ፤ በቅን ትፈርዳላችሁን? 2 የለም፤ በልባችሁ ክፋትን ታውጠነጥናላችሁ፤ በእጃችሁም ዐመፅን በምድር ላይ ትጐነጒናላችሁ። 3 ክፉዎች…

መዝሙር 59

ክፉዎችን በመቃወም የቀረበ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ “አታጥፋ” በሚለው ቅኝት የሚዜም፤ ዳዊትን ለመግደል ሰዎች ቤቱን ከብበው እንዲጠብቁት ሳኦል በላካቸው ጊዜ፤ የዳዊት ቅኔ 1 አምላክ ሆይ፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ፤ ሊያጠቁኝ ከሚነሡብኝም ጠብቀኝ። 2 ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤ ደም…

መዝሙር 60

ከሽንፈት በኋላ የቀረበ ብሔራዊ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ “የኪዳን ጽጌረዳ”። በሚለው ቅኝት የሚዘመር፤ በሰሜናዊ ምዕራብ መስጴጦምያና በማእከላዊ ሶርያ የሚኖሩትን አራማውያን በወጋቸው ጊዜ፣ ኢዮአብም ተመልሶ በጨው ሸለቆ አሥራ ሁለት ሺህ ኤዶማውያንን በፈጀ ጊዜ፣ ለትምህርት፤ የዳዊት ቅኔ 1…

መዝሙር 61

የግዞተኛ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤ ጸሎቴንም አድምጥ። 2 ልቤ በዛለ ጊዜ፣ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ። 3 አንተ መጠጊያዬ፣ ከጠላትም የምተገንብህ…

መዝሙር 62

ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ብቻ ለመዘምራን አለቃ፤ ለኤዶታም፤ የዳዊት መዝሙር 1 ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ድነቴም የሚመጣልኝ ከእርሱ ዘንድ ነው። 2 ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም። 3 ሰውን የምታጠቁት…

መዝሙር 63

እግዚአብሔርን መፈለግ በይሁዳ ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ፤ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ከልብ እሻለሁ፤ ውሃ በሌለበት፣ በደረቅና በተራቈተ ምድር፣ ነፍሴ አንተን ተጠማች፤ ሥጋዬም አንተን ናፈቀች። 2 ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤ ኀይልህንና…