መዝሙር 64

የተሳዳቢዎች ቅጣት ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር 1 አምላክ ሆይ፤ የብሶት ቃሌን ስማ፤ ሕይወቴንም ከሚያስፈራ የጠላት ዛቻ ከልላት። 2 ከክፉዎች አድማ ሰውረኝ፤ ከዐመፀኞችም ሸንጎ ጋርደኝ። 3 እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤ መርዘኛ ቃላቸውንም እንደ ፍላጻ ያነጣጥራሉ።…

መዝሙር 65

የምስጋና መዝሙር ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት የምስጋና መዝሙር 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በጽዮን ለአንተ ውዳሴ ይገባል፤ ለአንተ የተሳልነውን እንፈጽማለን። 2 ጸሎትን የምትሰማ ሆይ፤ የሰው ልጆች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ። 3 ኀጢአት ባጥለቀለቀን ጊዜ፣ አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ።…

መዝሙር 66

የኅብረት ምስጋና ለመዘምራን አለቃ፤ ማኅሌት፤ መዝሙር 1 ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል ይበል! 2 ለስሙ ክብር ዘምሩ፤ ውዳሴውንም አድምቁ 3 እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው! ጠላቶችህ ከኀይልህ ታላቅነት የተነሣ፣ በፊትህ ይርዳሉ። 4 ምድር ሁሉ…

መዝሙር 67

የመከር ጊዜ መዝሙር ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር፤ ማኅሌት 1 እግዚአብሔር ይማረን፤ ይባርከን፤ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ሴላ 2 መንገድህ በምድር ላይ፣ ማዳንህም በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይታወቅ ዘንድ። 3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ ሰዎች ሁሉ ምስጋና…

መዝሙር 68

ብሔራዊ የድል መዝሙር ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር፤ ማኅሌት 1 እግዚአብሔር ይነሣ፤ ጠላቶቹ ይበተኑ፤ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ። 2 ጢስ እንደሚበንን፣ እንዲሁ አብንናቸው። ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣ ክፉዎችም እንዲሁ ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ። 3 ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤…

መዝሙር 69

እንጒርጒሮ ለመዘምራን አለቃ፤ በ“ጽጌረዳ” ዜማ፤ የዳዊት መዝሙር 1 አምላክ ሆይ፤ አድነኝ፤ ውሃ እስከ ዐንገቴ ደርሶብኛልና። 2 የእግር መቆሚያ በሌለው፣ በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ሰጥሜአለሁ፤ ወደ ጥልቅ ውሃ ገባሁ፤ ሞገዱም አሰጠመኝ። 3 በጩኸት ደከምሁ፤ ጉሮሮዬም ደረቀ፤ አምላኬን…

መዝሙር 70

የጭንቀት ጩኸት ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር፤ ለመታሰቢያ 1 አምላክ ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ዘንበል በል፤ እግዚአብሔርሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን። 2 ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ፣ ይፈሩ፤ ሁከትም ይምጣባቸው፤ የእኔን መጐዳት የሚመኙ፣ በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ። 3 በእኔ ላይ፣…

መዝሙር 71

የሽማግሌ ጸሎት 1 እግዚአብሔርሆይ፤ አንተን መጠጊያ አደረግሁ፤ ከቶም አልፈር። 2 በጽድቅህ ታደገኝ፤ አስጥለኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም። 3 ምንጊዜም የምሸሽበት፣ መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ አንተ ዐለቴ ምሽጌ ነህና፣ ታድነኝ ዘንድ ትእዛዝህ ይውጣ። 4 አምላኬ ሆይ፤…

መዝሙር 72

በተስፋ የሚጠባበቀው ንጉሥ ስለ ሰሎሞን 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍትህን ለንጉሥ፣ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ ዐድል፤ 2 እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ ይዳኛል፤ ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል። 3 ተራሮች ብልጽግናን፣ ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ። 4 ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤ የድኾችን…

መዝሙር 73

የፍትሕ አሸናፊነት የአሳፍ መዝሙር 1 እግዚአብሔር ልባቸው ንጹሕ ለሆነ፣ ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው! 2 እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ። 3 ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣ በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና። 4 አንዳች ጣር የለባቸውም፤ ሰውነታቸውም ጤናማና…