መዝሙር 84

ወደ መቅደሱ ጒዞ መዝሙር ለመዘምራን አለቃ፤ በዋሽንት የሚዜም የቆሬ ልጆች መዝሙር 1 የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ ማደሪያህ ምንኛ የተወደደ ነው! 2 ነፍሴየእግዚአብሔርንአደባባዮች ትናፍቃለች፤ እጅግም ትጓጓለታለች፤ ልቤና ሥጋዬም፣ ለሕያው አምላክ እልል በሉ። 3 ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት አምላክ…

መዝሙር 85

ለሰላም የቀረበ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች፤ መዝሙር 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤ የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ። 2 የሕዝብህን በደል ይቅር አልህ፤ ኀጢአታቸውንም ሁሉ ሸፈንህ።ሴላ 3 መዓትህን ሁሉ አራቅህ፤ ከብርቱ ቍጣህም ተመለስህ። 4 መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ…

መዝሙር 86

የመከራ ጊዜ ጸሎት የዳዊት ጸሎት 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል፤ ስማኝም፤ እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና። 2 ለአንተ የተለየሁ ሰው ነኝና ነፍሴን ጠብቃት፤ አንተ አምላኬ ሆይ፤ በአንተ የታመነብህን ባሪያህን አድን። 3 ጌታ ሆይ፤ ማረኝ፤ ቀኑን…

መዝሙር 87

ጽዮን የሕዝቦች እናት የቆሬ ልጆች መዝሙር፤ ማሕሌት 1 መሠረቱን በተቀደሱ ተራሮች አቆመ፤ 2 እግዚአብሔርከያዕቆብ ማደሪያዎች ሁሉ ይልቅ፣ የጽዮንን ደጆች ይወዳል። 3 የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤ ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ሴላ 4 “ከሚያውቁኝ መካከል፣…

መዝሙር 88

ሰቆቃ ማሕሌት፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር፤ ለመዘምራን አለቃ፤ በማኸላት የሚዘመር፤ የይዝራኤላዊው የኤማን ትምህርት 1 አዳኜ የሆንህ አምላክእግዚአብሔርሆይ፤ በቀንና በሌሊት በፊትህ አጮኻለሁ። 2 ጸሎቴ በፊትህ ትድረስ፤ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፤ 3 ነፍሴ በመከራ ተሞልታለችና፤ ሕይወቴም ወደ ሲኦልተቃርባለች።…

መዝሙር 89

መዝሙርና ለእግዚአብሔር ታማኝነት የቀረበ ጸሎት የይዝራኤላዊው የኤታን ትምህርት 1 ስለእግዚአብሔርምሕረት ለዘለላለም እዘምራለሁ፤ በአፌም ታማኝነትህን ከትውልድ እስከ ትውልድ እገልጻለሁ። 2 ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት፣ ታማኝነትህንም በሰማይ እንደምታጸና እናገራለሁና። 3 አንተም እንዲህ ብለሃል፤ “ከመረጥሁት ጋር ኪዳን ገብቻለሁ፤ ለባሪያዬ…

መዝሙር 90

የሰው ልጅ ሕይወት የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት 1 እግዚአብሔርሆይ፤ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን። 2 ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣ ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣ አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ። 3 ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤ “የሰው…

መዝሙር 91

የእግዚአብሔር ጥበቃ 1 በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ ሁሉን በሚችል አምላክጥላ ሥር ያድራል። 2 እግዚአብሔርን፣“መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ። 3 እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣ ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና። 4 በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።…

መዝሙር 92

ጻድቅ ሰው ሲደሰት በሰንበት ቀን የሚዘመር መዝሙር፤ ማሕሌት 1 እግዚአብሔርንማመስገን መልካም ነው፤ ልዑል ሆይ፤ ለስምህ መዘመር ጥሩ ነው፤ 2 ምሕረትህን በማለዳ፣ ታማኝነትህንም በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፤ 3 ዐሥር አውታር ባለው በገና፣ በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ…

መዝሙር 93

የእግዚአብሔር ግርማ 1 እግዚአብሔርነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔርግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም። 2 ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ። 3 እግዚአብሔርሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤ ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤…