ምሳሌ 14

1 ጠቢብ ሴት ቤቷን ትሠራለች፤ ተላላ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች። 2 አካሄዱ ቅን የሆነ ሰውእግዚአብሔርንይፈራል፤ መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ይንቀዋል። 3 የተላላ ሰው ንግግር ለጀርባው በትር ታስከትልበታለች፤ የጥበበኛ ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። 4 በሬዎች በሌሉበት…

ምሳሌ 15

1 የለዘበ መልስ ቊጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቊጣን ይጭራል። 2 የጠቢብ አንደበት ዕውቀትን ታወድሳለች፤ የተላሎች አንደበት ግን ቂልነትን ያፈልቃል። 3 የእግዚአብሔርዐይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፤ ክፉዎችንም ደጎችንም ነቅተው ይመለከታሉ። 4 ፈውስ የምታመጣ ምላስ የሕይወት ዛፍ…

ምሳሌ 16

1 የልብ ዕቅድ የሰው ነው፤ የአንደበት መልስ ግንከእግዚአብሔርዘንድ ነው። 2 ለሰው መንገዱ ሁሉ ንጹሕ መስሎ ይታየዋል፤ መነሻ ሐሳቡ ግንበእግዚአብሔርይመዘናል። 3 የምታደርገውን ሁሉለእግዚአብሔርዐደራ ስጥ፤ ዕቅድህም ሁሉ ይሳካልሃል። 4 እግዚአብሔርሁሉንም ነገር ለራሱ ዐላማ ሠርቶአል፤ ክፉዎችንም እንኳ ለጥፋት…

ምሳሌ 17

1 ጠብ እያለ ግብዣፈ ከሞላበት ቤት ይልቅ፣ በሰላምና በጸጥታ የእንጀራ ድርቆሽ ይሻላል። 2 ጠቢብ አገልጋይ በወራዳ ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ ከወንድማማቾቹም እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል። 3 ማቅለጫ ለብር፣ ከውር ለወርቅ ነው፤ እግዚአብሔርግን ልብን ይመረምራል። 4…

ምሳሌ 18

1 ወዳጅነትን የማይፈልግ ሰው የራሱን ፍላጎት ብቻ ይከተላል፤ ቅን የሆነውን ፍርድ ሁሉ ይቃወማል። 2 ተላላ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤ የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል። 3 ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤ ከዕፍረትም ጋር ውርደት ትመጣለች። 4 ከሰው…

ምሳሌ 19

1 ንግግሩ ጠማማ ከሆነ ዐጒል ሰው ይልቅ፣ ያለ ነውር የሚሄድ ድኻ ሰው ይሻላል። 2 ዕውቀት አልባ የሆነ ቀናዒነት መልካም አይደለም፤ ጥድፊያም መንገድን ያስታል። 3 ሰው በራሱ ተላላነት ሕይወቱን ያበላሻል፤ በልቡ ግንእግዚአብሔርንያማርራል። 4 ሀብት ብዙ ወዳጅ…

ምሳሌ 20

1 የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤ በእነዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም። 2 የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፤ የሚያስቈጣውም ሰው ሕይወቱን ለመከራ ይዳርጋል። 3 ከጠብ መራቅ ለሰው ክብሩ ነው፤ ተላላ ሁሉ ግን ለጥል…

ምሳሌ 21

1 የንጉሥ ልብበእግዚአብሔርእጅ ነው፤ እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሰኘው ይመራዋል። 2 ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤ እግዚአብሔርግን ልብን ይመዝናል። 3 ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣ በእግዚአብሔርዘንድ ተቀባይነት አለው። 4 ትዕቢተኛ ዐይን፣ እብሪተኛ ልብ፣ የክፉዎችም…

ምሳሌ 22

1 መልካም ስም ከብዙ ብልጽግና ይመረጣል፤ መከበርም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል። 2 ባለጠጋና ድኻ የሚጋሩት ነገር፣ እግዚአብሔርየሁላቸውም ፈጣሪ መሆኑ ነው። 3 አስተዋይ ሰው አደጋ ሲያይ መጠጊያ ይሻል፤ ብስለት የጐደለው ግን በዚያው ይቀጥላል፤ መከራም ያገኘዋል። 4 ትሕትናናእግዚአብሔርንመፍራት፣…

ምሳሌ 23

1 ከገዥ ጋር ለመብላት በምትቀመጥበት ጊዜ፣ በፊትህ ያለውን በሚገባአስተውል፤ 2 ስግብግብም ብትሆን እንኳ፣ በጒሮሮህ ላይ ካራ አጋድምበት፤ 3 የእርሱ ጣፋጭ መብል አያስጐምጅህ፤ ምግቡ አታላይ ነውና። 4 ሀብት ለማግኘት ስትል ራስህን አታድክም፤ ሐሳብህን የመግታት ጥበብ ይኑርህ።…