ኢሳይያስ 43

የእስራኤል ብቸኛ አዳኝ 1 አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ! የፈጠረህ፤ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤ 2 በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣…

ኢሳይያስ 44

የተመረጠው እስራኤል 1 “ነገር ግን አሁንም ባሪያዬ ያዕቆብ፣ የመረጥሁህ እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ 2 የፈጠረህ፣ በማሕፀን የሠራህ፣ የሚረዳህ፣ እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ባሪያዬ ያዕቆብ፣ የመረጥሁህ ይሹሩን ሆይ፣ አትፍራ። 3 በተጠማ ምድር ላይ ውሃ፤ በደረቅ መሬት ላይ ወንዞችን አፈሳለሁና፤…

ኢሳይያስ 45

1 “ለቀባሁት፣ ቀኝ እጁን ለያዝሁት፣ ነገሥታትን ትጥቅ አስፈታ ዘንድ፣ ሕዝብን ሁሉ ላስገዛለት፣ ደጆች እንዳይዘጉ፣ በሮቹን በፊቱ ለምከፍትለት፣ ለቂሮስእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ 2 ‘በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራሮችንእደለድላለሁ፤ የናስ በሮችን እሰብራለሁ፤ የብረት መወርወሪያዎችንም እቈርጣለሁ። 3 በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ፣ እኔእግዚአብሔርመሆኔን…

ኢሳይያስ 46

የባቢሎን አማልክት 1 ቤል ተዋረደ፤ ናባው እጅግ ዝቅ አለ፤ ጣዖቶቻቸው በአጋሰስ ተጭነዋል፤ ይዘዋቸው የሚዞሩት ምስሎች ሸክም ናቸው፤ ለደከሙ እንስሳት ከባድ ጭነት ናቸው። 2 እነርሱም በአንድ ላይ ዝቅ ይላሉ፤ ያጐነብሳሉ፤ ጭነቱን ለማዳን አይችሉም፤ ራሳቸውም በምርኮ ይወሰዳሉ።…

ኢሳይያስ 47

የባቢሎን ውድቀት 1 “አንቺ የባቢሎንድንግል ልጅ ሆይ፤ ውረጂ፤ በትቢያ ላይ ተቀመጪ፤ አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ከዙፋንሽ ውረጂ፤ መሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ውብ ወይም ለግላጋ፣ ተብለሽ አትጠሪም። 2 ወፍጮ ወስደሽ እህል ፍጪ፤ መሸፋፈኛሽን አውልቂ፤ ቀሚስሽንም ከፍ…

ኢሳይያስ 48

እልከኛዪቱ እስራኤል 1 “የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እናንት በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፣ ከይሁዳ ዘር የተገኛችሁ፣ እናንትበእግዚአብሔርስም የምትምሉ፣ በእውነት ወይም በጽድቅ ሳይሆን፣ የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ ይህን ስሙ! 2 እናንት የቅድስቲቱ ከተማ ነዋሪዎች ነን ብላችሁ ራሳችሁን የምትጠሩ፣ በእስራኤል አምላክ…

ኢሳይያስ 49

የእግዚአብሔር ባሪያ 1 እናንት ደሴቶች ስሙኝ፤ እናንት በሩቅ ያላችሁ ሕዝቦች ይህን አድምጡ፤ በእናቴ ማሕፀን ሳለሁእግዚአብሔርጠራኝ፤ ከመወለዴ በፊት በስም ጠራኝ። 2 አፌን እንደ ተሳለ ሰይፍ አደረገው፤ በእጁ ጥላ ሰወረኝ፤ የተወለወለ ፍላጻ አደረገኝ፤ በሰገባውም ውስጥ ሸሸገኝ። 3…

ኢሳይያስ 50

የእስራኤል ኀጢአትና የእግዚአብሔር ባሪያ ታዛዥነት 1 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺ ወረቀት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥኋችሁ ለየትኛው አበዳሪዬ ነው? እነሆ፤ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁ ተፈታለች። 2 በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም?…

ኢሳይያስ 51

የዘላለም ድነት ለጽዮን 1 “እናንት ጽድቅን የምትከታተሉ፣ እግዚአብሔርንየምትፈልጉ ስሙኝ፤ ተቈርጣችሁ የወጣችሁበትን ዐለት፣ ተቈፍራችሁ የወጣችሁባትንም ጒድጓድ ተመልከቱ። 2 ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፣ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሣራ ተመልከቱ፤ በጠራሁት ጊዜ አንድ ራሱን ብቻ ነበር፤ ባረክሁት፤ አበዛሁትም። 3…

ኢሳይያስ 52

1 ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ኀይልን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ! የክብር ልብስሽን ልበሺ፤ ያልተገረዘ የረከሰም ከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም። 2 ትቢያሽን አራግፊ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ በዙፋንሽ ላይ ተቀመጪ፤ ምርኮኛዪቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ የዐንገትሽን የእስራት…