ዳንኤል 2
ናቡከደነፆር ያለመው ሕልም 1 ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አለመ፤ መንፈሱ ታወከ፤ እንቅልፍም ከእርሱ ራቀ። 2 ያለመውንም ሕልም እንዲነግሩት ንጉሡ ጠንቋዮችን፣ አስማተኞችን፣ መተተኞችንና ኮከብ ቈጣሪዎችንእንዲጠሩ አዘዘ፤ እነርሱም ገብተው በፊቱ ቆሙ፤ 3 እርሱም፣ “አንድ ሕልም አለምሁ፤…
ናቡከደነፆር ያለመው ሕልም 1 ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አለመ፤ መንፈሱ ታወከ፤ እንቅልፍም ከእርሱ ራቀ። 2 ያለመውንም ሕልም እንዲነግሩት ንጉሡ ጠንቋዮችን፣ አስማተኞችን፣ መተተኞችንና ኮከብ ቈጣሪዎችንእንዲጠሩ አዘዘ፤ እነርሱም ገብተው በፊቱ ቆሙ፤ 3 እርሱም፣ “አንድ ሕልም አለምሁ፤…
የወርቁ ምስልና የእቶን እሳት 1 ንጉሡ ናቡከደነፆር ከፍታው ሥልሳ ክንድ፣ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው። 2 ከዚያም መኳንንትን፣ ሹማምትን፣ አገረገዦችን፣ አማካሪዎችን፣ የግምጃ ቤት ኀላፊዎችን፣ ዳኞችን፣ ሌሎች የሕግ ዐዋቂዎችንና…
ናቡከደነፆር በሕልሙ ዛፍ አየ 1 ከንጉሥ ናቡከደነፆር፣ በምድር ሁሉ ለሚኖሩ ሕዝቦች፣ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን ለሚናገሩ ሰዎች ሁሉ፤ ሰላም ይብዛላችሁ! 2 ልዑል አምላክ ያደረገልኝን ታምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ሥራዎች ስነግራችሁ እጅግ ደስ እያለኝ ነው። 3 ምልክቱ…
በግድግዳው ላይ የታየው ጽሕፈት 1 ንጉሥ ቤልሻዛር ለሺህ መኳንንቱ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ በሺሁም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር። 2 ቤልሻዛር የወይን ጠጁን እየጠጣ ሳለ፣ አባቱናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ያመጣቸውን የወርቅና የብር መጠጫዎችን እርሱና መኳንንቱ፣ ሚስቶቹና…
ዳንኤል በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ 1 ዳርዮስ በመንግሥቱ ሁሉ ላይ እንዲገዙ አንድ መቶ ሃያ መሳፍንትን መሾም ፈለገ፤ 2 በእነዚህም ላይ ሦስት የበላይ አስተዳዳሪዎችን አደረገ፤ ከእነርሱም አንዱ ዳንኤል ነበረ። ንጉሡ ጒዳት እንዳይደርስበት፣ መሳፍንቱ ተጠሪነታቸው ለሦስቱ የበላይ አስተዳዳሪዎች…
ዳንኤል ስለ አራቱ አራዊት ያየው ሕልም 1 የባቢሎን ንጉሥ ቤልሻዛር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በዐልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልም አለመ፤ ራእይም አየ፤ የሕልሙንም ዋና ሐሳብ ጻፈው። 2 ዳንኤል እንዲህ አለ፤ “አራቱ የሰማይ ነፋሳት ታላቁን ባሕር…
ዳንኤል በራእዩ ያየው አውራ በግና ፍየል 1 ንጉሥ ቤልሻዛር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ አስቀድሞ ከተገለጠልኝ ራእይ በኋላ እኔ ዳንኤል ሌላ ራእይ አየሁ። 2 በራእዩም፣ በኤላም አውራጃ በሱሳ ግንብ ራሴን አየሁት፤ በራእዩም በኡባል ወንዝ አጠገብ ነበርሁ፤ 3…
የዳንኤል ጸሎት 1 የሜዶናዊው የአርጤክስስልጅ ዳርዮስ በባቢሎንበነገሠ በመጀመሪያው ዓመት፣ 2 በዘመነ መንግሥቱ በመጀመሪያው ዓመት፣ እኔ ዳንኤል ለነቢዩ ለኤርምያስ በተሰጠውየእግዚአብሔርቃል መሠረት፣ የኢየሩሳሌም መፈራረስ ሰባ ዓመት እንደሚቈይ ከቅዱሳት መጻሕፍት አስተዋልሁ። 3 ስለዚህ ማቅ ለብሼ፣ በራሴም ላይ ዐመድ…
ዳንኤል በራእይ ያየው ሰው 1 የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ ብልጣሶር ለተባለው ዳንኤል ራእይ ታየው። መልእክቱ እውነት ነው፤ ስለ ታላቅ ጦርነትም የሚገልጽ ነበረ። መልእክቱንም ይገነዘብ ዘንድ በራእይ ማስተዋል ተሰጠው። 2 በዚያን ጊዜ እኔ ዳንኤል…
1 እኔም፣ ሜዶናዊው ዳርዮስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት፣ እርሱን ለማገዝና ለማበረታታት በአጠገቡ ቆሜ ነበር። የሰሜንና የደቡብ ነገሥታት 2 “አሁንም እውነቱን እነግርሃለሁ፤ እነሆ፣ ሦስት ሌሎች ነገሥታት በፋርስ ይነሣሉ፤ አራተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል። በባለጠግነቱም እጅግ…