ዮናስ 3

ዮናስ ወደ ነነዌ ሄደ 1 የእግዚአብሔርምቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ ዮናስ መጣ፤ 2 “ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ የምነግርህን መልእክት ስበክላት።” 3 ዮናስምየእግዚአብሔርንቃል ታዘዘ፤ ወደ ነነዌም ሄደ። በዚህ ጊዜ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤…

ዮናስ 4

ዮናስ እግዚአብሔር ምሕረት በማድረጉ ተቈጣ 1 ዮናስ ግን ፈጽሞ አልተደሰተም፤ ስለዚህም ተቈጣ። 2 ወደእግዚአብሔርምእንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “እግዚአብሔርሆይ፤ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁትስ ይህን አልነበረምን? ፈጥኜ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል የተነሣሁትም ለዚሁ ነበር፤ አንተ ቸርና ርኅሩኅ፤ ምሕረትህ የበዛ ከቍጣ…

ሚክያስ 1

1 በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣውየእግዚአብሔርቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፤ 2 እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ሁላችሁም ስሙ፤ ምድር ሆይ፤ በውስጧም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፤ ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣…

ሚክያስ 2

የእግዚአብሔርና የሰው ዕቅድ 1 ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና። 2 ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤ ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤ የሰውን ቤት፣ የባልንጀራን ርስት አታልለው ይወስዳሉ። 3 ስለዚህእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤…

ሚክያስ 3

መሪዎችና ነቢያት ተገሠጹ 1 ከዚያም እኔ እንዲህ አልሁ፤ “እናንት የያዕቆብ መሪዎች፤ እናንት የእስራኤል ቤት ገዦች ስሙ፤ ፍትሕን ማወቅ አይገባችሁምን? 2 መልካሙን ጠላችሁ፤ ክፉውንም ወደዳችሁ፤ የሕዝቤን ቈዳ ገፈፋችሁ፤ ሥጋቸውንም ከዐጥንቶቻቸው ለያችሁ፤ 3 የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ፤ ቈዳቸውን…

ሚክያስ 4

የእግዚአብሔር ተራራ 1 በመጨረሻው ዘመን፣ የእግዚአብሔርቤተ መቅደስ ተራራ፣ ከተራሮች ልቆ ይታያል፤ ከኰረብቶች በላይ ከፍ ይላል፤ ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ። 2 ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደእግዚአብሔርተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንሂድ፤ በመንገዱ እንድንሄድ፣ መንገዱን…

ሚክያስ 5

ከቤተ ልሔም ገዥ እንደሚመጣ የተሰጠ ተስፋ 1 አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤ ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤ ከበባ ተደርጎብናልና፤ የእስራኤልን ገዥ፣ ጒንጩን በበትር ይመቱታል። 2 “አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ ከይሁዳ ነገዶችመካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ አመጣጡከጥንት፣ ከቀድሞ ዘመንየሆነ፣ የእስራኤል…

ሚክያስ 6

የእግዚአብሔር ክስ በእስራኤልን ላይ 1 እግዚአብሔርየሚለውን ስሙ፤ “ተነሡ፤ ጒዳያችሁን በተራሮችም፤ ፊት አቅርቡ፤ ኰረብቶች እናንተ የምትሉትን ይስሙ፤ 2 ተራሮች ሆይ፤የእግዚአብሔርንክስ አድምጡ፤ እናንት የምድር ጽኑ መሠረቶችም፤ ስሙ፤ እግዚአብሔርከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፤ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳል። 3 “ሕዝቤ ሆይ፤…

ሚክያስ 7

የእስራኤል መከራ 1 ለእኔ ወዮልኝ! የወይን ዕርሻ በሚቃረምበት ጊዜ የበጋ ፍራፍሬ እንደሚለቅም ሰው ሆኛለሁ፤ የሚበላ የወይን ዘለላ የለም፤ የምንጓጓለት፣ ቶሎ የሚደርሰው በለስም አልተገኘም። 2 ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበት ሰው ከምድር ጠፍቶአል፤ አንድም እንኳ ቅን ሰው የለም፣…

ናሆም 1

1 ስለ ነነዌ ጥፋት የተነገረ ንግር፤ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው፤ በነነዌ ላይ የተገለጠ የእግዚአብሔር ቍጣ 2 እግዚአብሔርቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔርየሚበቀል፣ በመዓትም የተሞላ ነው። እግዚአብሔርባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ በጠላቶቹም ላይ ቍጣውን ያመጣል 3 እግዚአብሔርለቍጣ የዘገየ…